የኩሉ እሴቶች

ተአማኒነት/እውነታ

ኩሉ ኔትዎርክ በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ትክክለኛና በእውነታ ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን ለማስተላለፍ ይተጋል፡፡ ትክክለኛነት እና እውነታ ከፕሮግራም ጥራት በላይ እጅግ ተፈላጊ መሆኑን እናምናለን፡፡ የምናገኛቸውን እያንዳንዱን መረጃዎች በማመዛዘን እና ትክክለኛነቱን  በማረጋገጥ እውነታን እናገኛለን፡፡ በኩሉ ኔትወርክ የሚሰራጩ ማንኛውም አይነት  መረጃዎችም በወጉ የተጠኑ እንዲሁም እውነተኛ ምንጭ ያላቸው ናቸው፡፡ አቀራረባቸውም አጠር ያለና በግልፅ ቋንቋ የሚቀርብ ነው፡፡ ስለማናውቃቸው ጉዳዮች አለማወቃችንን በግልፅ ለተመልካቾቻችን እናስታውቃለን፡፡ ኩሉ ምንጭ ያልተገኘላቸውን መረጃዎች ፈፅሞ አያቀርብም፡፡ 

የመረጃ እኩልነት

ኩሉ ኔትዎርክ በሚያቀርባቸው መረጃዎች ላይ በሀሳብ እኩልነት ያምናል፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የሃሳብ ልዩነቶችና ግጭቶችን መርምሮ እኩል በሆነ መልኩ ያንፀባርቃል፡፡ እያንዳንዱን የምናነሳቸውን ጉዳዩችም ከአላማችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም እናቀርባለን፡፡ የተለያዩ ሙያዊ ግምገማዎችን በመስጠት በአመክንዮ የተደገፈ ሂስ የምንሰጥ ሲሆን የአንዱን ሀሳብ አንስተን የሌላውን ጥለን አናበላልጥም፡፡ በተጨማሪም አከራካሪና አነጋጋሪ የሆኑ ፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች በፕግራሞቻችን ላይ አይካተቱም፡፡

የዝግጅት አቋምና ነፃነት

ኩሉ ኔትዎርክ ነፃ የሆነ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም ነው፡፡ ነጻ የሆነ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም መሆናችንን ተመልካቾቻችን እንዲረዱ አሰራራችን ተመልካቾቻችን የሚረዱበት ግልፅ አሰራር ዘርግተናል፡፡  ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች ውጫዊ አካላት የሚደርስ ተፅኖን በመቋቋም የግል አሰራር የሚንፀባረቅበት ይሆናል፡፡

የህዝብን ፍላጎት ማሟላት

ኩሉ ኔትዎርክ ምንግዜም የሚያቀርባቸው ፕሮግራሞች በእውነታ ላይ የተመሰረቱ እና ተጨባጭ ጉዳዮችን ነው፡፡ ታሪኮቹ ላይም ጥልቅ ምርምርና ጥናት በማድረግ ለህዝብ ተደራሽ ይሆናሉ፡፡ ይህን ውስብስብ የሆነውን አለማችንን ቀላልና ግልፅ በሆነ መልኩ ለማቅረብ በሙያው የካበተ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ አጥጋቢ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘትም ሰፊ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቦታዎችን በመዳሰስ እንዲሁም ውይይቶችን በማሰናዳት ይተገበራል፡፡

ፍትሀዊነት

ኩሉ ኔትዎርክ አገልግሎቶችን ግልፅ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመስጠት የተዘጋጀ ተቋም ነው፡፡ ስለሆነም ፕሮግረራሞች እንዲሁም ግለሰቦች በቅንነትና እኩልነት ይስተናገዳሉ፡፡

ነፃነት

ኩሉ ኔትዎርክ በዋነኛነት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች አንዱ ነፃነት ነው፡፡ አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜያት ይህ ነፃነት የማይተገበርበት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ግልፅ በሆነ መልኩ የማህበረሰብ ፍላጎቶችን በማጥናት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዘገባ እና ትንታኔ የምንሰጥ ይሆናል፡፡ 

አካላዊና ስነ አእምሯዊ እክሎች/ጉዳቶች

ኩሉ ኔትዎርክ ዋነኛ አላማ የገሀዱን አለም ትክክለኛ ገፅታ ተአማኒነት ባለው መንገድ ማቅረብ ሲሆን የሚቀርቡ ማናቸውም መረጃና ጉዳዮች ለህዝብ ከመተላለፋቸው በፊት በማህበረሰባችን ላይ ሊያደርሰውን የሚችለውን አካላዊና ስነአእምሯዊ ተጽእኖዎች በቅድሚያ በመገምገም የእርማት ስራዎችን እንሰራለን፡፡  

ህፃናት

ኩሉ ኔትዎርክ ምንግዜም ቢሆን ለህፃናትና ታዳጊዎች ስነ ልቦናዊ ጤንነት ይጠነቀቃል፡፡ ስለሆነም የህጻናት መብት በመላው አለም መከበር አለበት ይላል፡፡ ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ኩሉ ኔትዎርክ የሚያስተላልፋቸውን ፐሮግራሞች ህጻናትና ታዳጊዎችን ባማከለ መልኩ በተለያየ መስፈርት የፕሮግራም ክፍለጊዜን ያዘጋጃል፡፡

ተጠያቂነት/ ሀላፊነት መውሰድ

ኩሉ ኔትወርክ ምንግዜም ለተመልካቾች ለሚያቀርባቸው ፕሮግራሞች/መልዕክቶች ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ከታዳሚዎች ጋርም ግልፅና ተመጣጣኝ በሆነ መልኩም መስተጋብርን ይፈጥራል፡፡ በህዝብና በኩሉ ኔትዎርክ መሀከልም ቀጣይነት ያለው መተማመንን መፍጠር ዋና አላማችን ነው፡፡ በመሆኑም ስህተታችንን እና ጉድለታችንን በመቀበል የማሻሻያ አርምጃዎችን እንወስዳለን፡፡

 

  • space.png
Website Developed by Rafatoel Advertising & Events